ብዙ ሰዎች ብልት ወይም የግል ሰውነት ክፍሎች ቆዳ (የውጭ ብልት አካባቢ, ብሽሽት እና ጭን ) ከመሳሰሉት ቦታዎች ሲጠቁር ምቾት አይሰማቸውም። የግል ሰውነት ክፍሎች ቀለም መቀየር ( hyperpigmentation) ተፈጥሯዊ ሲሆን መልካም ዜናው ሊስተካከል የሚችል ሁኔታ ነው ።
ለመሆኑ የግል ሰውነት ክፍሎች ቀለም መቀየር ( hyperpigmentation) ምንድን ነው ?
የግል ሰውነት ክፍሎች ቀለም መቀየር ( Intimate hyperpigmentation) ማለት የግል ሰውነታችን አካባቢ ማለትም የውጭ ብልት ፣ ብሽሽት እና ጭን አካባቢ የ ሚከሰት ጥቁረት ሲሆን የሚከሰተው ከመጠን በላይ በሆነ ሜላኒን የሰውንተታችን ሆርሞን ምርት ምክንያት ነው። ሜላኒን ለቆዳ እና ለፀጉር ቀለም ምክንያት የሚሆን ሆርሞን ነው። ለምሳሌ ጥቁሮች ከነጮች የሚለዩት ብዙ ሜላኒን ሳላላቸው ነው። እንዲሁም በተወሰኑ የ ሰውንተታችን ቦታዎች ላይ ካለው ወፍራም ቆዳ ምክንያት(የውጭ ብልት አካባቢ, ብሽሽት), ቆዳው ከትክክለኛው ይልቅ ጥቁር እንዲመስል ሊያደርገው ይችላል።
የግል ሰውነት ክፍሎች ጥቁረት( hyperpigmentation ) የተለመዱ ምክንያቶች
1. እድሜ፡- ዕድሜያችን እየገፋ ሲሄድ የቆዳችን ቅርጽ፣ የመለጠጥ፣ የመሸብሸብ፣ ቀለም የመቀየር ባህሪ ያሳያል፤ ይህም በሰውነት ክፍሎቻችን ላይ ጥቁር ጠባሳ ሊያስከትል ይችላል።
2. መተሻሸት፡- በተለይ በብሽሽት እና በውስጥ ጭን ላይ ያለማቋረጥ የቆዳ መተሻሸት ቆዳ እንዲጠቁር ያደርገዋል ጠባብ ልብስ, ተደጋጋሚ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የቆዳ መተሻሸት የሚጨምሩ ምክንያቶች ናቸው።
3. የሆርሞን ለውጦች፡- የሆርሞኖች መለዋወጥ በተለይም በእርግዝና ወቅት ፣ ቆዳው እንዲጠቁር ሊያደርግ ይችላል።
4. ደጋግሞ መላጨት፡- አዘውትሮ መላጨት ቆዳን እንዲጠቁር ያደርገዋል። ከተላጨ በኋላ በአዲስ ፀጉር እድገት ምክንያት የሚመጣ መተሻሸት ለ hyperpigmentation አስተዋጽኦ ያደርጋል።
5. የአየር ዝውውር አለመኖር:- ጠባብ ልብስ ወይም የውስጥ ሱሪ መልበስ አየር እንዳይዘዋወር ያደርጋል፤ ይህም እርጥበት እንዲከማችና ቆዳው እንዲጠቁር ያደርገዋል።
የግል ሰውነት ክፍሎች የቆዳ ቀለም መቀየርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
● ጠባብ ልብሶችን አዘውትሮ አለመልበስ
● አዘውትሮ መላጨት ማስወገድ
● ላብ የሚመጥ ልብሶችን መልበስ
በቤት ውስጥ ሚዘጋጁ መፍትሄወች
- የኮኮናት ዘይት እና የሎሚ ጭማቂ
አዘገጃጀት
- ከ 2-3 የሾርባ ማንኪያ የኮኮናት ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
- በደንብ እስከሚዋሃዱ በደንብ ማዋሃድ
አጠቃቀም
- የተዘጋጀውን ውህድ ጥቁረት በደረሰበት ቦታ መቀባት
- ከ 10-15 ደቂቃዎች በሗላ መታጠብ
2. የኦትሜል (አጃ) ማጽጃ
አዘገጃጀት
- ከ 2-3 የሾርባ ማንኪያ አጃ
- ከ 2-3 የሾርባ ማንኪያ እርጎ
- 1 የሻይ ማንኪያ ማር
- በደንብ እስከሚዋሃዱ በደንብ ማዋሃድ
አጠቃቀም
- የተዘጋጀውን ውህድ ጥቁረት በደረሰበት ቦታ መቀባት
- ከ 10-15 ደቂቃዎች በሗላ መታጠብ
3. የድንች ማጽጃ
አጠቃቀም
- አንድ ቁራጭ ጥሬ ድንች በጠቆረው ቆዳ ላይ ለ15 ደቂቃ መቀባት
- መታጠብ
ድንች ጥቁረት ለማጥፋት የሚረዳ ካቴኮላዝ የተባለ ኢንዛይም በውስጡ ይዟል።
የቤት ውስጥ ውህዶች በቂ ካልሆኑ፣ በክሬሞች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። እነዚህ ምርቶች በተለምዶ እንደ ሃይድሮኩዊኖን፣ ሬቲኖይክ አሲድ፣ ኮጂክ አሲድ እና አዜላይክ አሲድ ያሉ ንጥረ ነገሮችን ይይዛሉ።
Product Recommendation
1. The Ordinary Azelaic Acid Suspension 10%
2. Dermamelan Intimate. This chemical peel is specifically formulated for intimate areas
and has shown success in reducing skin discoloration.
3. Obagi Nu-Derm Clear Fx
4. SkinCeuticals Retinol 1.0 Maximum Strength Refining Night Cream
5. MelanoLyte Pigment Perfecting Serum
6. Ambi Skincare Fade Cream
7. Paula’s Choice 1% Retinol Treatment
8. Koji White Kojic Acid Skin Brightening Soap
9. Paula’s Choice 10% Azelaic Acid Booster
የግል ሰውነት ክፍሎች ጥቁረት የተለመደ ነው እና በተገቢው እንክብካቤ ሊጠፋ ይችላል። የተለየ ህመም እና አላርጅክ ካለባችው የቆዳ ሐኪም አማክሩ ።
References:
● Goldstein, Andrew. “Preventing and Treating Intimate Skin Discoloration.” WebMD, Link.
● “How to Lighten Dark Skin in Intimate Areas.” Healthline, Link.
● “Top Home Remedies for Intimate Hyperpigmentation.” Medical News Today, Link.
● American Academy of Dermatology: Hyperpigmentation Treatment
● Healthline: How to Lighten Dark Skin in Intimate Areas