rice water

ፀጉር ሳይበጣጠስ እና ሳይሰባበር እንዲያድግ የሚረዳ ተፈጥሯዊ የሩዝ ውሃ

የሩዝ ውሃ በቤትሽ ውስጥ በማዘጋጀት ወዝ ያለው የዞማ ፀጉር ባለቤት ሴት መሆን ትችያለሽ። በፍጥነት ለውጥ ሊያሳይሽ የሚችለው ይህ ተፈጥሯዊ ውህድ በጥንታዊቷ የቻይና ዩአንግሎ ከተማ በያዎ ሴቶች የተገኘ ሁነኛ የፀጉር ማሳደጊያ መንገድ እንደሆነ ይነገራል።

የሩዝ ውሃ ለፀጉር እድገት የሚሰጣቸው ጥቅሞች

  • ሩዝ “vitamins, minerals, antioxidants እና amino acids” በውስጡ በመያዙ ፀጉር ጤነኛ እና ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል።
  • የሩዝ ውሃ “Starch” ስለሚያካትትም የሚያንፀባርቅ የፀጉር ባለቤት እንድትሆኚ ያስችላል።
  • ለፀጉር እድገትና ብዛት ሁነኛ መፍትሄ እንደሆነ የሚመሰከርለትም በውስጡ “Inositol” ስለያዘ ነው።

የሩዝ ውሃ አሰራር

ግብዓቶች

  • አንድ የሻይ ብርጭቆ ሩዝ
  • የብርቱካን ወይም የሎሚ ልጣጭ
  • የቀረፋ አንጨት፣ የጥብስ ቅጠል ወይም በተለምዶ የሮዝሜሪ ቅጠል (እንደ አማራጭ)

አዘገጃጀት

  • ሩዙ ቆሻሻ ሊኖረው ስለሚችል በትንሹ ማጠብ
  • ለማዘጋጀት የምትፈልጊውን መጠን ያክል ውሃ ሩዝ ጋር መጨመር
  • የታጠበ የብርቱካን ወይም ሎሚ ልጣጭ ቆራርጠሽ ማስገባት
  •  ሁሉንም አንድ ላይ በጣም በትንሹ ማፍላት
  • በጣም በትንሹ ሲፈላ ወደማጠራቀሚያ ጨምረሽ ለ24 ሰዓት ከድነሽ ማስቀመጥ
  • ሩዙን ከውሃው በማጥለል ውሃውን ለመጠቀም መዘጋጀት

አጠቃቀም

  •  የተዘጋጀውን የሩዝ ውሃ የውስጡም የውጪውም የፀጉርሽ ክፍል እስኪዳረስ ድረስ ማሳጅ እያደረግሽ የሩዙን ውሃ መቀባት።
  • ሞይስቸራይዝ ለማድረግ ቅባት መጠቀም።

አንዳንድ ነጥቦች

  • የሩዝ ውሃ እጅግ ብዙ ፕሮቲን ስለሚኖረው የፀጉር ልስላሴ እጥረት ሊያጋጥምሽ ስለሚችል በሳምንት 2 እስከ 3 ጊዜ ብቻ ብትጠቀሚው ይመረጣል።
  • በየቀኑ የምትቀቢ ከሆነ ደግሞ የሩዝ ውሃ ከተጠቀምሽ በኋላ ሞይስቸራይዝ ለማድረግ ቅባት ብትቀቢ መልካም ነው።
  • አንድ ጊዜ ብቻ የመጠቀም እድል ካለሽ ደግሞ ፀጉርሽ በጣም እስኪረስ ድረስ የሩዙን ውሃ በመቀባት ከዛም ለአንድ ሰዓት አቆይተሽ መታጠብ እና ቅባት መቀባት ይመከራል።
  • ይሄንን ውህድ ለመስራት የሚያስችል ግብዓቶች ከሌለሽ ሌሎች ሴፍስኮዬር ያዘጋጀለሽን ውህዶች መሞከር።
 

ስለ ሩዝ ውሃ ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

1.የሩዝ ውሃ ላይ የብርቱካን ወይም የሎሚ ልጣጭ ለምን እጠቀማለሁ?

የሩዝ ውሃ በተፈጥሯዊ መንገድ ስለሚዘጋጅ ሽታ ሊኖረው ይችላል። ይሄንንም ሽታ ለመከላከል ሲባል የብርቱካን ወይም የሎሚ ልጣጭ መጠቀም አስፈላጊ ነው። እነዚህ ከሌሉሽም የቀረፋ አንጨት፣ የጥብስ ቅጠል ወይም በተለምዶ የሮዝሜሪ ቅጠል የሚባሉትን መጠቀም ትችያለሽ።

2. የሩዝ ውሃ ብቻ ብጠቀም ምን ይፈጠርብኛል?

የበለጠ የፀጉር እድገት እንዲኖር ፀጉርን መንከባከብ ያስፈልጋል። ለአንድ ሳምንት ያክል የሩዙን ውሃ ከተጠቀምሽ በኋላ በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ሌሎች በሙዝ፣ በሽንኩርት ፣ አቮካዶ ወዘተ የሚዘጋጁ የፀጉር ማሳደጊያዎችን መጠቀም ለውጡ ቶሎ እንዲጨምር ይረዳል።

3.  ሞይስቸራይዝ ለማድረግ የትኛውን ቅባት ልቀባ?

የሩዝ ውሃ ብዙ ፕሮቲን ስላለው ፀጉርን የግድ መንከባከብና ማለስለስ ያስፈልጋል። ለማለስለስ ወይም ሞይስቼራይዝ ለማድረግ ከተገኘ የኮኮኖት Oil ካላገኘሽ እስከዛሬ የምትጠቀሚውንና የሚመችሽን የፀጉር ቅባት መጠቀም ትችያለሽ።

4. የሩዝ ለሁሉም የፀጉር አይነት ይሆናል?

የሩዝ ውሃ ከርዳዳ ፀጉር ያላቸው ሴቶች ሲጠቀሙት እንዳልሰራላቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማል።

5. ለምን ያክል ጊዜ የሩዙን ውሃ ልቀባ?

እንደ ፀጉርሽ እና እንዳንቺ ፍላጎት ቢለያይም በየቀኑ ለሳምንት ያክል ማሳጅ አድርገሽ እየተቀባሽ ከዛም ሞይስቸራይዝ ለማድረግ ቅባት ብትቀቢ መልካም ነው።

6. እርጉዝ ሴት ብትጠቀመው ችግር አለው?

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እርግዝና ላይ ያለች ሴት ብትጠቀመው ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው ነው። የተሻለ መረጃ ለማግኘት ደግሞ የህክምና ባለሙያዎችን / ዶክተሮችን / ማማከሩ ይመረጣል

Tags: No tags

Comments are closed.