የከንፈር ቀለም ሳይጠፋ ረጅም ጊዜ እንዲቆይ የሚያደርጉ መንገዶች

የምትቀቢው ሊፒስቲክ ወይም የከንፈር ቀለም እንዳይለቅብሽ የሚያደርጉ የተለያዩ መፍትሄዎችን በመጠቀም ውበቱን መጠበቅ ትችያለሽ።

የተለያዩ የ”Eye Liner” አይነቶች

  1. ከንፈሮችሽ ላይ Dead skin cells ወይም በአማርኛ የሞቱ የቆዳ ሴሎች የሚባሉትን ለማጥፋትና ለስላሳና ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በመጀመሪያ በLip ስክረብ አልያም በጥርስ ቡርሽሽ ከንፈርሽን በስሱ መጥረግ።

 

2. ሊፕ ላይነር ተጠቀሚ። ከሊፕስቲክ ቀለም ጋር የሚመሳሰል አልያም ጠቆር ያለ ሊፕ ላይነር በመጠቀም የምትቀቢው ሊፕስቲክ ከመስመሩ እንዳይወጣ ያግዝሻል።

 

3. ሊፒስቲክ ስትቀቢ ሁለት ጊዜ ብትደርቢው ይመረጣል። ይሄም ረዘም ላለ ጊዜ ሊፒስቲኩ ከንፈርሽ ላይ እንዲቆይ ያስችለዋል። ታዲያ ሁለተኛውን ለመደረብ የመጀመሪያው ከደረቀ በኋላ መሆኑ አትርሺ።

 

4. Translucent Powder መጠቀም። ከተቀባሽ በኋላ በስሱ ይሄንን ፓውደር ከንፈርሽ ላይ ካደረግሽ ሊፒስቲኩ ልብስሽ ላይ፣ መነፀርሽ ላይ፣ ቆዳ ላይ ሲነካካ ምስል እንዳይተው ከማድረጉ ባሻገር ረዘም ላለ ጊዜም እንዲቆይልሽ ይረዳል።

 

የተለያዩ የአሳሳል ስታይሎች

  1. ገና ሊፒስቲክሽን እንደተቀባሽ ዘይት ነገር ያላቸውን ምግብ እና መጠጦች አትጠቀሚ።
  2. ብዙ ጊዜ የሚያልብሽ ከሆነ ደግሞ በላብና በእርጥበት ላይ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ተደርገው የተሰሩ Long-wear ሊፒስቲኮችን ተጠቀሚ።
  3. ሊፒስቲክ ስትገዢ የከንፈርሽ ሼፕ ምን አይነት እንደሆነ መጀመሪያ ብታውቂ በጣም ይመረጣል። 
  4. ከቆዳሽ ቀለም ጋር የሚሄድ ሊፒስቲክ መጠቀምም የበለጠ ውብ ያደርግሻል።
Tags: No tags

Comments are closed.