ብጉር ከወጣ በኋላ የፊትሽ ቆዳ ላይ የሚቀሩት ጥቋቁር ነጠብጣቦች በቀላሉ ይሄን የድንች ክሬም በመጠቀም ማጥፋት ትችያለሽ። ፍክት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት አሪፍ መፍትሄ ከመሆኑም ባሻገር ተፈጥሯዊ መሆንም በብዙ ሴቶች እንዲመረጥና እንዲወደድ አስችሎታል።
ድንች ለፊት ቆዳ የሚሰጣቸው ጥቅሞች
ብጉር ከወጣ በኋላ የፊትሽ ቆዳ ላይ የሚቀሩት ጥቋቁር ነጠብጣቦች በቀላሉ ይሄን የድንች ክሬም በመጠቀም ማጥፋት ትችያለሽ። ፍክት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት አሪፍ መፍትሄ ከመሆኑም ባሻገር ተፈጥሯዊ መሆንም በብዙ ሴቶች እንዲመረጥና እንዲወደድ አስችሎታል።
- ድንች Azelaic Acid በውስጡ በመያዙ ጥቋቁር ነጠብጣቦችን በማደብዘዝ የፊት ቆዳ ፍክት እንዲል ያደርጋል።
- Antibacterial ስለሆነም ድንች ብጉር እንዳይባባስ የማድረግ አቅም አለው።
- Antibacterial ስለሆነም ድንች ብጉር እንዳይባባስ የማድረግ አቅም አለው።
የድንች የፊት ክሬም አሰራር
ግብዓቶች
- አንድ በትንሹ ብቻ የተቀቀለ / ያልበሰለ መካከለኛ መጠን ድንች
- አንድ ያልተቀቀለ ድንች
- በጣም ጥቂት ሎሚ
አዘገጃጀት
- በትንሹ የተቀቀለውን ልጠሽ መከታተፍ
- ያልተቀቀለውን ድንች በመፈቅፈቅ ከዛም በደንብ እየተጫንሽ ውሃውን ለማውጣት መሞከር
- 2 የሾርባ ማንኪያ የተፈቀፈውን ድንች ተቀቅሎ ከበሰለው ድንች ጋር ማደባለቅ
- ያልተቀቀለው ድንች ላይ የወጣውን ውሃ ጨምሮ ድንቹን መፍጨት
- ክሬም እስኪመስል ድረስ ድንቹን እየፈጩ መቆየት (ከወፈረብሽ እጅግ ጥቂት የሎሚ ጭማቂ ወይም ውሃ መጨመርና ድጋሚ መፍጨት)
አጠቃቀም
- ፊትን በሳሙና/ውሃ ታጥበሽ ማደራረቅ
- የደረቀ ፊት ላይ ይሄንን ክሬም መቀባት
- ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት ተቀብቶ መቆየት
- መታጠብ
አንዳንድ ነጥቦች
- ድንች ለረጅም ሰዓት ላይ ለአንዳንድ ሰዎች የቆዳ መቆጣት ሊያመጣ ይችላል።
- ለፊትሽ ቆዳ አላርጂክ ከሆነ መሞከር የለብሽም።
- ለፀሀይ የበለጠ ሴንሴቲቭ ሊያደርግ ስለሚችል ድንች ከተጠቀምሽ በኋላ ሰንስክሪን ሊያስፈልግ ይችላል።
- በየቀኑ መቀባት የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ ያስችላል።
- ሎሚ ከበዛ የፊት መቆጣት ሊያመጣ ስለሚችል እንዳይበዛብሽ ተጠንቀቂ። አላርጂክ ካለብሽም ማስገባት የለብሽም።
- ይሄንን ውህድ ለመስራት የሚያስችል ግብዓቶች ከሌለሽ ሌሎች ሴፍስኮዬር ያዘጋጀለሽን ውህዶች መሞከር።
ስለ ድንች ክሬም ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች
- ለስንት ጊዜ ተሰርቶ መቀመጥ ይችላል? ፍሪጅ ውስጥ ሲገባስ አይበላሽም?
የድንች ክሬም ተሰርቶ ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ ይችላል። ነገር ግን የሚከተሉት ነገሮችን ልብ ማለት ያስፈልጋል።
- በንፁህ የፍሪጁ ቦታ ላይ አስቀምጪው
- ማስኩን በሰራሺው ወዲያውኑ ካልቻልሽ ደግሞ ከ2 እስከ 3 ቀናት ባሉት ውስጥ መጠቀም መጀመር አለብሽ።
- የመበላሸት ባህሪ እንደ መጥቆር፣ መሻገት የመሳሰሉትን ነገር ካየሽ መጣል አለብሽ።
2. ወዲያው እየጠቆረብኝ ተቸገርኩ። ምን ላድርግ?
ድንች የተፈጥሮ ግብዓት በመሆኑ ምክንያት በተለያዩ መንስኤዎች ሊበላሽ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ በፍጥነት ሲበላሽ፣ አንዳንዴም ለረጅም ጊዜ ሲቆይ ይስተዋላል። ይሁን እንጂ ከመበለሻት የምናድንበት እርግጠኛው መፍትሄ ለአንድ ቀን የሚሆንሽን ክሬም በማዘጋጀት ነው። ለእለት ተእለት የሚሆን በትንሹ እየሰራሽ መጠቀም የተሻለ አማራጭ ነው።
3. ይሄን የፊት ማስክ ሳዘጋጅ የግድ ሎሚ መጨመር አለብኝ?
የለብሽም! በተለይ በብዙ መጠቀም የፊት መቆጣት ሊያስከትልብሽ ይችላል። ነገርግን ክሬሙን ስታዘጋጂ እና ሲወፍርብሽ በጣም ጥቂት የሎሚ ጭማቂ መጨመር ጥቅም እንድታገኚበትም ያስችላል። ሎሚ በውስጡ “Vitamin C” ስለያዘ ቆዳን ከመጎዳት ከመጠበቁ ባሻገር በቆዳ ላይ የሚፈጠሩ ጥቋቁር ነጠብጣቦች ለማጥፋት ይረዳል። አስታውሺ! ሎሚም ሆነ ሌሎች ግብዓቶች አላርጂክ ካለብሽ መቆጠቡ ይመረጣል።
4. በምን ያክል ጊዜ ለውጥ ላገኝ እችላለሁ?
በየቀኑ የተቀቡት ሴቶች በሳምንት ውስጥ ለውጥ እንዳዩ ተናግረዋል።
5. ጥቋቁር ነጠብጣቦች ከጠፉልኝ በኋላ ክሬሙ ማቆም እችላለሁ?
ከጠፋልሽ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ከምታቆሚው የምትጠቀሚበትን ጊዜ እየቀነሽ ቢሆን ጥሩ ነው። ለምሳሌ በየቀኑ እየተቀባሽ ከሆነ ሲጠፋልሽ በሶስት ቀን አንዴ መቀባት ትችያለሽ።
6. ተቀብቼ መተኛት እችላለሁ?
ትችያለሽ። ነገር ግን ትራስ እንዳያበላሽብሽ ተጠንቀቂ እንዲሁም የትራስ ልብስሽ ንፁህ መሆኑንን በደንብ እርግጠኛ መሆን አለብሽ። ነገር ግን ጊዜ ካለሽ ከ1 እስከ 2 ሰዐት አቆይተሽ መታጠቡ ይመረጣል።