foot

ተረከዝ እንዳይሰነጣጠቅ እና እንዳይሻክር የሚረዳ ተፈጥሯዊ ውህድ

ይሄንን ክሬም በቤትሽ ውስጥ በማዘጋጀት ተረከዝሽን ለስላሳ ማድረግ የምትችይ ሲሆን ለማዘጋጀትም በጣም ቀላል መሆኑ በብዙ ሴቶች እንዲመረጥ ብሎም እንዲወደድ አስችሎታል።

ይህ ውህድ ለሻከረና ለተሰነጣጠቀ ተረከዝ የሚሰጣቸው ጥቅሞች

  • ሎሚ በውስጡ “Alpha-Hydroxy Acids (AHAs)” ስለያዘ የሞቱ የቆዳ ሴሎችን በማስወገድ አዳዲስ ሴሎች እንዲመረቱ/እንዲታደሱ ይረዳል።
  • ቫዝሊን “Petroleum Jelly” ስለሆነ ቆዳ እርጥበት እንዲኖረው እና የመሰነጣጠቅ ባህሪን እንዲቀንስ የሚወጣም ነው።
  • ኮኮናት ኦይል ተፈጥሯዊ ሞይስቼራይዘር/አለስላሽ/ ተብሎ የሚጠራም ሲሆን በ “Fatty Acids” የበለፀገ ነው። ይሄም የማለስለስ ባህሪያት እንዲኖሩት አስችሎታል።

የክሬሙ አሰራር

ግብዓቶች

  • ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ቫዝሊን
  • ግማሽ ሎሚ
  • ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ኮኮናት Oil

አዘገጃጀት

  • ከላይ የተጠቀሱትን ግብዓቶች በሙሉ አንድ ላይ መቀላቀል
  • ሎሚውና ቫዝሊኑ ይበልጥ እንዲቀላቀልና የበለጠ እንዲዋሃድ በጣም በትንሹ እሳት ላይ ሞቅ ማድረግ

አጠቃቀም

  • የተዘጋጀውን ክሬም የሻከረና የተሰነጣጠቀው የተረከዝ ቦታ ላይ ቀቢው
  • ከዛም ካልሲ በማድረግ መተኛት/ የእለት ተእለት ክንውናኔሽ መቀጠል

አንዳንድ ነጥቦች

  • በዛ ያለ ሎሚ መጠቀም የቆዳ መቆጣት ሊያመጣብሽ ይችላል።
  •  ሴንሴቲቭ ቆዳ ካለሽ በትንሽ ቦታ ላይ ሞክሪውና የማያቃጥልሽ ከሆነ ክሬሙን መጠቀም መቀጠል ትችያለሽ።
  • የተረከዝ መሰንጠቁ እጅግ ብዙ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎችን/ዶክተሮችን ማማከር አስፈላጊ ነው።
  • ይሄንን ውህድ ለመስራት የሚያስችል ግብዓቶች ከሌለሽ ሌሎች ሴፍስኮዬር ያዘጋጀለሽን ውህዶች መሞከር።
 

ስለዚህ ክሬም ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

1.ሎሚና ቫዝሊኑን የበለጠ ለማቀላቀል ምን ያክል እሳት ላይ ማቆየት አለብኝ?

እስከሚቀላቀል ብቻ በጣም በጥቂቱ እሳት ላይ ማድረግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። Microwave ካላችሁ ደግሞ እስከ 15 ሰከንድ ገደማ ያክል ሞቅ ማድረግ ይበቃል።

2. ካልሲ ማድረጌ ጥቅሙ ምንድን ነው?

ካልሲ የቆዳ እርጥበት እንዳይተን ስለሚያደርግ ለስላስ ተረከዝ እንዲኖር ያስችላል። እንዲሁም በፍትጊያ ምክንያት የሚከሰት የቆዳ ድርቀትን ስለሚከላከል ተመራጭ ነው። ይሄን የተፈጥሮ ክሬም ከተጠቀምሽ በኋላ ደግሞ ካልሲ ማድረግሽ ውህዱ/መድሃኒቱ ይበልጥ ሰርፆ እንዲገባና ለውጡ በጣም ፈጣን እንዲሆን ያስችላል።

3. ተረከዝ ለምን ይሰነጣጠቅብኛል?

ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ብርድ፣ እንክብካቤ አለመስጠት፣ ማለስለሻ አለመጠቀም፣ ረጅም ጊዜ ሩጫ ላይ ማሳለፍ ወዘተ ይጠቀሳሉ።

Tags: No tags

Comments are closed.