nail

ጥፍርሽን ውብ እና ጠንካራ ለማድረግ 

ጥፍርሽን ውብ እና ጠንካራ ለማድረግ 

ጥፍርሽ እየተሰባበረ እና ውበቱ እየቀነሰ ከተቸገርሽ የሚከተለውን መንገድ በመከተል ማራኪና ለአይን የሚያሳሳ ጠንካራ ጥፍር የሚኖርሽ ይሆናል።

ሎሚ እና ኦሊቭ ኦይል “(የወይራ ዘይት) Olive Oil” ለጥፍር የሚሰጧቸው ጥቅሞች

  • በ”Olive Oil” ውስጥ የሚገኘው “Fatty Acids” ጥፍር እንዳይሰባበር እና በጥንካሬነቱ እንዲቆይ ያደርጋል።
  • “Olive Oil” በጥፍር ውስጥ የሚገኙትን የጥፍር ሴሎች በማነቃቃት የጥፍር እድገት እንዲኖር ያስችላል።
  • እንደ “Vitamin E” ያሉ “AntiOxidants” በውስጡ ስለያዘም “Olive Oil” ጥፍር እንዳይጎዳ የማድረግ አቅም አለው።
  • ሎሚ የ “Antifungal” ባህሪያት በውስጡ ስላለው ጥፍር በፈንገስ እንዳይጠቃ ያግዛል።
  • “Vitamin C” ሎሚ ውስጥ ይገኛል ፤ ይሄም ጥፍር እንዲጠነክርና የመሰባበር እድሉን እንዲቀንስ ያደርጋል።

የሎሚ ውህድ አሰራር

ግብዓቶች

  • ግማሽ ሎሚ
  • ሶስት የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት “Olive Oil”

አዘገጃጀት

  • ሶስት የሾርባ ማንኪያ ገደማ የሚጠጋ የወይራ ዘይት (Olive Oil) የምታዘጋጂበት ሰሃን ላይ ጨምሪ።
  • ግማሽ ሎሚ ጨምቀሽ አንድ ላይ ማደባለቅ

አጠቃቀም

  • ለ10 ደቂቃ ያክል ጥፍሮችሽን ውህዱ ውስጥ ነክሮ መጠበቅ
  • ጥፍሮችሽን እያንዳንዱን ለተወሰነ ደቂቃ ማሸት
  • ለ30 ደቂቃ ያክል ወይም ለሊቱን በሙሉ ማሳደር
  • ጥፍርን መታጠብ እና ማደራረቅ

አንዳንድ ነጥቦች

  • በየቀኑ መጠቀም የተሻለ ለውጥ ለማግኘት ያስችላል።
  • ፍሪጅ ውስጥ በማስገባት መጠቀምም ትችያለሽ።
  • ሴንሴቲቭ ቆዳ ካለሽ ሎሚውን በውሃ በትንሹ መበረዝ የተሻለ ነው።
  • ይሄንን ውህድ ለመስራት የሚያስችል ግብዓቶች ከሌለሽ ሌሎች ሴፍስኮዬር ያዘጋጀለሽን ውህዶች መሞከር።
Tags: No tags

Comments are closed.