የ”EYE LINER” የአሳሳል ስታይሎች June 18, 2024 EyesMakeup ብዙ ጊዜ ተዘውትረው የሚታዩት እነዚህን የ”Eye Liner” ስታይሎች መሞከር የአይን ውበትን የበለጠ ያጎናፅፋል። አንቺም እነዚህ ስታይሎች ካወቅሻቸው እሰየው ፤ ካልሆነ ግን እነሆ እንድታያቸው ጋበዝንሽ። 1. Classic Eyeliner : ቀላል ነገር ግን የሚያምር ስታይል ነው። ከላይኛው የአይን ሽፋሽፍትሽ ተነስተሽ መስመሩን ማስመር እና የአይን ቅድ መጨረሻ ላይ ክንፍ መሳይ (Winged) መልክ ማስያዝ ነው። 2. Cat Eyeliner : ቀልብ ገዢ የሆነው ይህ የአይላይነር ስታይል ወፈር አድርጎ ክንፍ መሳይ (Winged) ቅርፅ በማስያዝ መሳል ትችያለሽ። በሁለቱም የአይን ቅድ ላይ Winged መስመር ስለሚደረግም ማራኪ ያደርገዋል። 3. Smoky Eyeliner: ይህ የአይላይነር ስታይል ለስላስ ተደርጎ የሚሰራ ነገርግን ውጤቱ ቆንጆ የሚሆንም ነው። በአብዛኛው “Pencil Eyeliner” ወይም በ”Gel Eyeliner” ታግዞ የሚስራ ሲሆን የላይኛውን እና የታትኛውን የሽፋሽፍት መስመር ተክትሎ መሳል ምስሉ ላይ የሚታየውን አይነት እይታ ይፈጥርልናል። “Eye Shadow” በመጠቀምም የበለጠ ስዕሉን ማጉላት ይቻላል። 4. Graphic Eyeliner: ለየት ያለና የአሳሳል ጥበብ የሚፈልገው ይህ ስታይል በማንኛውም የአይላይነር አይነት መሳልም ይችላል። የተለያዩ ቅርፆች፣ ዲዛይኖችን በመስራት ለመጠበብም እድል ይፈጥራል። Previous Post ተረከዝ እንዳይሰነጣጠቅ እና እንዳይሻክር የሚረዳ ተፈጥሯዊ ውህድ Next Post የከንፈር ቀለም ሳይጠፋ ረጅም ጊዜ እንዲቆይ የሚያደርጉ መንገዶች