ጠባሳዎችን እንዴት ማከም ይቻላል? November 16, 2024 Personal CareSkin ጠባሳዎች ተፈጥሯዊ የፈውስ ሂደት ክፍል ናቸው፣ነገር ግን ገጽታቸውን ለመቀነስ ብዙ ዘዴዎች አሉ። ጠባሳዎች በቆዳዎ መካከለኛ ሽፋን ውስጥ የሚገኘው ኮላጅን፣ ኢላስቲን እና የደም ሥሮች ሲጎዱ የሚፈጠሩ ናቸው። በቃጠሎ፣ ቀዶ ጥገና፣ ብጉር ወይም ጉዳት ምክንያት በሚደርስ ቁስል ፈውስ ሂደት ውስጥ ይፈጠራሉ። ምርጥ ሕክምና ምንድን ነው? ለጠባሳዎች አንድ-መጠን-ሁሉንም-ይስማማ ተአምር መፍትሄ የለም፣ ምክንያቱም የተለያዩ ሕክምናዎች በተለያየ ደረጃ ይሻላሉ። ጠባሳዎች ሙሉ በሙሉ ባይጠፉም፣ ህክምና ገጽታቸውን ለመቀነስ ይረዳል። 1. ጊዜ እና ትዕግስት: ብዙውን ጊዜ ጠባሳዎች ከጊዜ በኋላ ይጠፋሉ። ቆዳዎ በተፈጥሮ ለመፈወስ በቂ ጊዜ ይስጡት። 2. ከፀሀይ ይጠበቁs: ጠባሳዎች ለፀሀይ መጋለጥ የለባቸውም በየቀኑ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም አስፈላጊ ነው። 3. Moisturizing: ጠባሳ ቆዳን እርጥበት እንዲያገኝ ማድረግ። ጠባሳውን በእርጥበት አዘል Moisturizer መቀባት የጠባሳ ቲሹን ለመስበር ይረዳል, ጠባሳውን በፍጥነት ያለሰልሳል። 4. ሲሊኮን ላይ የተመሰረቱ ምርቶች: ሲሊኮን ጄሎች መቅላትን ለመቀነስ እና የጠባሳዎችን ገጽታ ለማሻሻል ይረዳሉ። እርጥበትን በመጨመር ጠባሳዎችን ለማጠፍ ይረዳሉ። ነገር ግንውጤቶችን ለማየት ለበርካታ ወራት በቋሚነት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው። ውጤታማ የጠባሳ ሕክምና ምርቶች 1. Mederma Advanced Scar Gel በቃጠሎ፣ መቆረጥ፣ ቀዶ ጥገና እና ብጉርን ጨምሮ ለአዳዲስ እና ለድሮ ጠባሳዎች በደንብ ይሰራል።ውጤቶችን ለማየት ወራት ይወስዳል። 2. Derma-E Scar Gel ለተወሳሰቡ ጠባሳዎች፣ ለቃጠሎ እና ለስትሬች ማርክስ ጥሩ ነው። ውጤቶችን ለማየት ብዙ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። 3. ScarAway Silicone Scar Gel ለተለያዩ የጠባሳ ዓይነቶች ዉጤታማነቱ ተረጋግጧል። 4. Cica-Care Gel Sheet ለ C- section ጨምሮ ለቀዶ ጥገና ጠባሳዎች ተስማሚ። 5. Mederma for Kids ለህጻናት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ውጤቶችን ለማየት ወራት ይወስዳል። References: Healthline: How to Get Rid of Scars Healthline: Best Scar Creams Plastic Surgery Brisbane: Best Products for Scar Management WebMD: Treating Scars Previous Post Stretch Marks: ስትሬች ምልክቶችን መረዳት፡ መከላከል እና ማጥፋት