“Strawberry Legs” ተብሎ የሚጠራው ችግር ብዙውን ጊዜ ከቆዳ ላይ የሚወጣው ሌላ ዓይነት ቆዳ በሽታ ከሆነው ( keratosis pilaris )ጋር ይመሳሰላል። ይህ ችግር ቆዳ ላይ ያሉ ቀዳዳዎች በሞተ ቆዳ፣ ዘይትና ሌሎች ቆሻሻዎች ሲዘጉ የሚከሰት ነው። ይህም በእግርና በእጅ ላይ ጥቁር ነጠብጣቦች ወይም እንደ Strawberry የሚመስል ነጥቦች እንዲታዩ ያደርጋል። እነዚህ የተዘጉ ቀዳዳዎች በመላጨት፣ Waxing ወይም ጥብቅ (tight) ልብሶችን በመልበስ ምክንያት በሚፈጠረው ግጭት ሊባባሱ ይችላሉ።
“Strawberry Legs” በዋናነት በሦስት ምክንያቶች ይከሰታል፡
- የተዘጉ የቆዳ ቀዳዳዎች: ቆዳ ላይ ያሉ ቀዳዳዎች በሞተ ቆዳ፣ ዘይትና ሌሎች ቆሻሻዎች ሲዘጉ ኦክሳይድ ሲያደርግ ጥቁር ይሆናል ይህም ቆዳውን እንደ Strawberry ያለ ነጠብጣብ እንዲኖረው ያደርገዋል።
- በቆዳ ውስጥ የቀሩ ፀጉሮች: ብዙውን ጊዜ ተገቢ ያልሆነ የመላጨት ዘዴ ውጤት ነው፣ በቆዳ ውስጥ የቀሩ ፀጉሮች እብጠት ሊያስከትሉ ይችላሉ፣ ይህም የStrawberry እግር መልክን ያስከትላል።
- ፎሊኩላይተስ(Folliculitis): ይህ የፀጉር ሥር ባክቴሪያ ወይም ፈንገስ ኢንፌክሽን ነው፣ ይህም መቅላት፣ እና ቁስሎች ሊያስከትል ይችላል። ብዙውን ጊዜ በጥብቅ ልብስ ወይም ከመጠን በላይ ላብ ምክንያት የፀጉር ሥር ሲበሳጭ ይከሰታል።


እንዴት “Strawberry Legs” መከላከል ይቻላል
ትክክለኛ የሰውነት እንክብካቤ ልማድ በመጠቀም መከላከል ይቻላል። እነሆ እንዴት “የፍራፍሬ እግር” መከላከል እንደሚቻል፡
1. በትክክለኛ መንገድ ቆዳን መላጨት
ሹል መላጫ መጠቀም እና እርጥበት አዘል የመላጨት ክሬም መጠቀም የመላጨት ቁስሎችን እና በቆዳ ውስጥ የሚቀሩ ፀጉሮችን ይከላከላል። ሁልጊዜም ፀጉር በሚያድግበት አቅጣጫ መላጨት ቆዳን መቆጣትለመቀነስ ይረዳል።
Product Recommendation:
Aveeno Therapeutic Shave Gel: ይህ የመላጨት ጄል ለስላሳ መላጨት በማቅረብ በተመሳሳይ ጊዜ ቆዳን መቆጣት ለመቀነስ ይረዳል።
2. Keeping Skin Moisturized (ቆዳን እርጥበት እንዲያገኘኝ ማድረግ)
በደንብ እርጥበት ያገኘ ቆዳ “Strawberry Legs” የመያዝ ዕድሉ አነስተኛ ነው። ሽያ ቅቤ እና ሳሊሲሊክ አሲድ ( shea butter and salicylic acid )ያሉ እርጥበት አዘል ንጥረ ነገሮችን የያዘ ክሬም መጠቀም ቆዳን ለስላሳ እንዲሆን እና ደረቅነትን ይከላከላል።
Product Recommendation:
CeraVe SA Cream with Salicylic Acid for Rough & Bumpy Skin: ይህ ክሬም በቀስታ ቆዳን በማላላት ሞተው የሚወጣውን የቆዳ ሴሎች ክምችት በመከላከል እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል።
3. ደረቅ ብሩሽ
ደረቅ ብሩሽ ሞተው የሚወጣውን የቆዳ ሴሎችን በማስወገድ እና ቀዳዳዎችን መዘጋትን በመከላከል የሚረዳ አካላዊ ቆዳ ማላላት ዘዴ ነው። ገላዎን ከመታጠብዎ በፊት በደረቅ ቆዳ ላይ በክብ እንቅስቃሴ ይቦርሹ።
አጠቃቀም: ከእግርዎ ጀምሮ ወደ ላይ በመንቀሳቀስ በቀስታ በክብ እንቅስቃሴ ይቦርሹ።
Product Recommendation: ደረቅ ብሩሽ
4. በየጊዜው Exfoliate ማድረግ
Exfoliating የሞተው ቆዳን በማስወገድ ቀዳዳዎችን የሚዘጋውን ክምችት ይከላከላል። አልፋ-ሃይድሮክሳይድ አሲድ (AHA) እና ቤታ-ሃይድሮክሳይድ አሲድ (BHA) ያሉ የኬሚካል ቆዳ Exofoliate ለማድረግ በተለይ ውጤታማ ናቸው።
Product Recommendation:
First Aid Beauty KP Bump Eraser Body Scrub: ይህ ምርት ቆዳን ለስላሳ ለማድረግ እና ቀዳዳዎችን ንጹህ ለማድረግ አካላዊ እና ኬሚካላዊ ቆዳ ማላላትን ያጣምራል።
“Strawberry Legs” ከተከሰተ በኋላ….
ቀድሞውንም “Strawberry Legs” ካለብዎት በቀዳዳዎችን በማጽዳት እናበቆዳ ውስጥ የሚቀሩ ፀጉሮችን በመቀነስ ላይ ያተኩሩ።
Exfoliating Products
የሚፈለጉ ንጥረ ነገሮች: አልፋ-ሃይድሮክሳይድ አሲድ (AHA), ቤታ-ሃይድሮክሳይድ አሲድ (ሳሊሲሊክ አሲድ), ግላይኮሊክ አሲድ, ቫይታሚን ሲ, ሬቲኖይድስ.
Product Recommendation:
- The Ordinary Glycolic Acid 7% Toning Solution: የተዘጉ ቀዳዳዎችን ለማጽዳት እና የቆዳ ሸካራነትን ለማሻሻል የሚረዳ የኬሚካል ቆዳ ማላላት
- CeraVe SA Cream with Salicylic Acid for Rough & Bumpy Skin: ለጠባብ፣ ለተንቆጠቆ
- ጠ ቆዳ ሕክምና እና የ Strawberry Legs እንደገና መከሰት ለመከላከል ተስማሚ ነው።

Leg Mask
Leg Mask ቆዳን ለማረጋጋት እና Strawberry Legs መልክን ለመቀነስ ይረዳል።
የቤት ውስጥ Leg Mask አዘገጃጀት መመሪያ:
- ½ ኩባያ ሽምብራ ዱቄት
- ½ ኩባያ ሙሉ እርጎ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ማር
- ከ½ የሎሚ ጭማቂ
- ውሃ (ድብልቁ ወፍራም ውህድ እስኪፈጠር ድረስ በአንድ ጊዜ 1 የሾርባ ማንኪያ ይጨምሩ)
አጠቃቀም: Leg Maskን በእግርዎ ላይ ይቀቡት እና በሞቀ ውሃ ከመታጠብዎ በፊት ለ10-15 ደቂቃዎች ይተዉት። ይህ Mask ቆዳን ያስተካክላል፣ ያርጥባል እና ያረጋጋዋል።
Strawberry Legs ያበሳጫል፣ ነገር ግን ትክክለኛ የእንክብካቤ ልማድ በተሳካ ሁኔታ ሊታከም ይችላል። በቋሚነት ቆዳን Exofoliate ማድረግ፣ ትክክለኛ የመላጨት ዘዴዎች እና moisturize ማድረግ ይህንን ሁኔታ ለመከላከል እና ለማከም ቁልፍ ነው። እነዚህን ልምዶች በቋሚነት ከተከተሉ ቆዳዎ ለስላሳ እና ንጹህ ይሆናል።
References:
American Academy of Dermatology – Keratosis Pilaris
Gillette Venus – Strawberry Legs
Braun Female Hair Removal Guide