graphic_eyeliner

የ”EYE LINER” የአሳሳል ስታይሎች

ብዙ ጊዜ ተዘውትረው የሚታዩት እነዚህን የ”Eye Liner” ስታይሎች መሞከር የአይን ውበትን የበለጠ ያጎናፅፋል። አንቺም እነዚህ ስታይሎች ካወቅሻቸው እሰየው ፤ ካልሆነ ግን እነሆ እንድታያቸው ጋበዝንሽ።

1. Classic Eyeliner :  

ቀላል ነገር ግን የሚያምር ስታይል ነው። ከላይኛው የአይን ሽፋሽፍትሽ ተነስተሽ መስመሩን ማስመር እና የአይን ቅድ መጨረሻ ላይ ክንፍ መሳይ (Winged) መልክ ማስያዝ ነው።

classic
cat_eyeliner

2. Cat Eyeliner : 

ቀልብ ገዢ የሆነው ይህ የአይላይነር ስታይል ወፈር አድርጎ ክንፍ መሳይ (Winged) ቅርፅ በማስያዝ መሳል ትችያለሽ። በሁለቱም የአይን ቅድ ላይ Winged መስመር ስለሚደረግም ማራኪ ያደርገዋል። 

 

3. Smoky Eyeliner

ይህ የአይላይነር ስታይል ለስላስ ተደርጎ የሚሰራ ነገርግን ውጤቱ ቆንጆ የሚሆንም ነው። በአብዛኛው “Pencil Eyeliner” ወይም በ”Gel Eyeliner” ታግዞ የሚስራ ሲሆን የላይኛውን እና የታትኛውን የሽፋሽፍት መስመር ተክትሎ መሳል ምስሉ ላይ የሚታየውን አይነት እይታ ይፈጥርልናል። “Eye Shadow” በመጠቀምም የበለጠ ስዕሉን ማጉላት ይቻላል።

 

smoky_eyeliner
graphic_eyeliner

4. Graphic Eyeliner: 

ለየት ያለና የአሳሳል ጥበብ የሚፈልገው ይህ ስታይል በማንኛውም የአይላይነር አይነት መሳልም ይችላል። የተለያዩ ቅርፆች፣ ዲዛይኖችን በመስራት ለመጠበብም እድል ይፈጥራል።

 

Tags: No tags

Comments are closed.